Aktuell

Alpha-Kurs የደቀ መዝሙርነት ትምህርት

ከ 06.09.2026 ጀምረን አልፋ እና የደቀ መዝሙርነት ትምህርት እንሰጣለን

በግንቦት ወር የተጠመቁት 17 በቤተክርስቲያናችን የሚገኙ ወጣቶች በእምነታቸው ለማደግ እና የኢየሱስ ተከታዮች ሆነው ለመጓዝ አሁን የደቀ መዝሙርነት ትምህርት (Jüngerschaftskurs) ይጀምራሉ።

ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ወደ አዲሱ የአልፋ ኮርስ (Alpha-Kurs) ይጀምራል

የአልፋ ኮርስ ለማን የተዘጋጀ ነው?

በቤተክርስቲያናችን የሚገኙ ወጣቶች

ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት በላይ ለሆኑ በቤተክርስቲያናችን ለሚገኙ ወጣቶች ሁሉ።

እንግዶች እና ፈላጊዎች

ከ13 ዓመት በላይ ለሆኑ ስለ ክርስትና እምነት ለማወቅ እና ጥያቄዎቻቸውን እንዲመለስ ለሚፈልጉ ወጣቶች ሁሉ።

የኮርሱ መረጃ

የመጀመሪያ ቀን
ሰዓት
በየሳምንቱ እሑድ ከጠዋቱ 10:30 ሰዓት
ቦታ
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፍራንክፈርት (አጋፔ)
አድራሻ
Salzschlirfer Str. 7, 60386 Frankfurt am Main
መጓጓዣ
U-Bahn 4 & 7

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል – በደስታ እንጠብቃችኋለን!