ከቤተ ክርስቲያናችን አስደሳች ዜና አለን!
(May 09, 2026)
በቤተ ክርስቲያናችን ልዩና እጅግ አስደሳች የሆነ መንፈሳዊ ፕሮግራም ይኖረናል። በዚህ ዕለት፣ ከወጣቶች ኅብረታችን (AGAPE) 17 ወጣቶች የውሃ ጥምቀትን ይወስዳሉ። እነዚህ ወጣቶች ሕይወታቸውን ለጌታ አሳልፈው እንደሰጡና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያላቸውን ጥልቅ ኅብረት በጥምቀታቸው በአደባባይ ይመሰክራሉ።
ሌላ ታላቅ የምስራች!
በተመሳሳይ ቀን 16 የAGAPE ወጣቶች የደቀ መዝሙርነት ትምህርታቸውን (Jüngerschaftskurs) በተሳካ ሁኔታ አጠናቀው ይመረቃሉ። እነዚህ ወጣቶች ባለፉት ወራት የእግዚአብሔርን ቃል በጥልቀት ሲማሩ የቆዩ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የታመኑ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በመሆን በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ለመመላለስ ተዘጋጅተዋል።
በወጣቶቹ ሕይወት ውስጥ ስላለው የመንፈስ ቅዱስ ድንቅ ሥራ እግዚአብሔርን እጅግ እናመሰግናለን። መጥታችሁ ይህንን የተባረከ የቤተ ክርስቲያን ቀን ከእኛ ጋር እንድታከብሩ በጌታ ፍቅር እንጋብዛችኋለን!
Wundervolle Neuigkeiten!
Wir laden Sie herzlich zu einem ganz besonderen Gottesdienst ein. An diesem Tag werden 17 Jugendliche unserer AGAPE-Jugend die Wassertaufe empfangen. Mit diesem Schritt bezeugen sie mutig ihre tiefe Verbundenheit mit Jesus Christus.
Ein weiterer Grund zur Freude:
Zusätzlich feiern wir den erfolgreichen Abschluss des Jüngerschaftskurses von 16 weiteren jungen Menschen. Sie sind nun bereit, ihren Alltag als treue Jünger Jesu zu gestalten.
Wir sind dankbar für das Wirken des Heiligen Geistes. Kommen Sie und feiern Sie mit uns diesen gesegneten Tag der Gemeinde!
