የእምነት መሠረቶች
Glaubensgrundlagen
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ፍራንክፈርት
የእኛ መሠረቶች
Unsere Grundlagen
የእኛ መሠረቶች ማንነታችንንና ምን እንደሚያነሳሳን ይገልጻሉ። የክርስቶስን ተልዕኮ፣ የወደፊቱን ራዕያችንን እና ዓላማችንን ያካትታሉ።
ሰዎችን በፍቅሩ ወንጌል ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማምጣት እና እርሱን እስኪመስሉ ድረስ በቃሉ በማሳደግ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ማድረግ።
ወንጌልን ማሰራጨትየኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በፍራንክፈርት እና አካባቢው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ማሰራጨት።
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የታጠቀች፣ ለህብረተሰባችን ትርጉም ያለው ሁለንተናዊ አገልግሎትን የምትሰጥ ቤተ ክርስቲያን ሆና ማየት።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን የወንጌል ተልዕኮ መፈፀም፤ ቤተሰቦችን ማጠናከር እና አንድነትን ማሳደግ።
የእኛ እሴቶች
Unsere Werte
እሴቶቻችን የማህበረሰባችን ልብ ሲሆኑ፣ ለክርስቶስ እውነተኛ ምስክር ለመሆን በምናደርገው ጥረት ይመሩናል።
- ፍቅር: ያለ እውነተኛ ፍቅር ሕብረት እና አገልግሎት ከንቱ ነው።
- አንድነት: በመንፈስ የሚደረገውን አንድነት ለመጠበቅ እንተጋለን።
- ጴንጤቆስጤአዊነት: የመንፈስ ቅዱስን ኃይል እና ጥምቀት እናምናለን።
- ቅድስና: በሁሉም ነገር ጌታን ለመምሰል እንጥራለን።
- አጋርነት: ከሁሉም ዳግም ከተወለዱ አማኞች ጋር በአክብሮት እንሰራለን።
- ጾም እና ጸሎት: በጾምና በጸሎት ኃይልን እንቀበላለን።
- አገልጋይነት: እንደ ኢየሱስ ምሳሌ እርስ በርስ በትህትና እናገለግላለን።
- ፍትሕ: ለጽድቅ እና ለፍትሕ እንቆማለን።
- ግልጽነት: በእግዚአብሔር ቤት የምንሰራው ስራ ሁሉ ግልጽ መሆን አለበት።
የእምነት መግለጫ
Unser Glaubensbekenntnis
መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጻሕፍትን ያቀፈ፣ በመንፈስ ቅዱስ የተጻፈ፣ ከስህተት የጸዳና ሥልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው።
2.1 እግዚአብሔር አብ: ለዘላለም የመዳን ዕቅድ ፈጣሪ ነው።
2.2 እግዚአብሔር ወልድ: ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ነው።
2.3 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ: ዓለምን ስለ ኃጢአት የሚወቅስና አማኞችን የሚያጸና።
7.1 ድነት: ድነት የሚገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ነው።
7.5 ጥምቀት: ለአማኞች በውኃ ውስጥ ጥምቀትን እንተገብራለን።
7.11 ዳግም ምፅአት: የክርስቶስ ዳግም ምፅአት የአማኞች ተስፋ ነው።
አባልነት
Unsere Mitgliedschaft
የአባላት ግዴታዎች
Pflichten der Mitglieder
- የእምነት መግለጫውን መቀበል እና የቤተክርስቲያን ደንቦችን መታዘዝ።
- በአምልኮ፣ በጸሎት እና በስብሰባዎች ላይ በንቃት መሳተፍ።
- የእግዚአብሔርን ስራ በአስራትና በመባ በታማኝነት መደገፍ።
- በቃልና በሥራ የክርስቶስ መልእክተኛ ሆኖ ቅዱስ ሕይወት መኖር።
- የቤተክርስቲያን መሪዎችን ማክበርና መደገፍ።
ቤተ ክርስቲያን ለአባላት የምትሰጠው አገልግሎት
Dienste der Kirche an Mitglieder
- መደበኛ መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ ስልጠናዎች እና ኮንፈረንሶች።
- በሽታ፣ ሀዘን ወይም ችግር ውስጥ ላሉት መንፈሳዊ ድጋፍ መስጠት።
- የጋብቻ ስነ-ስርዓትና የህጻናት ባርኮት ማከናወን።
- የደቀ መዝሙርነት ትምህርት እና ወደ አገልግሎት ማስገባት።
