
መጋቢ እሸቱ ጉርሙ እባላለሁ።
የተወለድኩት በሰፕቴምበር 1952 ሲሆን በቀድሞ አጠራር በአርሲ ክፍለ ሐገር ስሬ ከሚባል ከተማ አካባቢ በሚገኝ መንደር ነው።
እጅግ የምወዳት ባለቤቴ እመቤት አሩሲ በሞት የተለየችኝ ሲሆን ጌታ ጽዮን እሸቱ፣ ሩት ጉርሙ እና ግሬስ ጉርሙ በሚባሉ ውድ ልጆች ባርኮኛል። ትምህርትና ጥሪ፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በአሰላ ከተማ የጨረስኩ ሲሆን፣ የእንሰሳት ሐኪም (ዶክተር) በመሆን የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን አጠናቅቄአለሁ።
ጌታ ኢየሱስ ለመንግስቱ ሥራ እንደጠራኝ ሳረጋግጥ በጀርመን ጴንጤቆስጤ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት (BFP) የነገረ መለኮት ትምህርት ወስጄ በሴፕቴምበር 2010 በመጋቢነት ተሾሜአለሁ። የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ፍራንክፈርት ከተመሰረተችበት ከኤፕሪል 1990 ጀምሮ በታማኝነት ያገለገልሁ ሲሆን ከጃኗሪ 2012 ጀምሮ ደግሞ የቤተ ክርስቲያንዋ መጋቢ በመሆን እያገለገልኩ እገኛለሁ።
የውስጥ ረሃቤ እና ናፍቆቴ በቤተ ክርስቲያናችን የእግዚአብሔር ክብር ተገልጦ ብዙዎች እንዲድኑ፣ የዳኑት ደግሞ እውነተኛ የየሱስ ደቀመዝሙር እንዲሆኑና ሁላችንም በጋራ በመንፈስና በእውነት ጌታን እንድናመልክ ነው።

