የፊልጵስዩስ መልዕክት ጥናት

የፊልጵስዩስ መልዕክት ጥናት

ምን ጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ!

ጸሓፊ

ሐዋርያ ጳውሎስ

ጊዜ

60–63 ዓ.ም

ቦታ

ሮም

ዓላማ

በእምነታቸው ጸንተው በክርስቶስ በአንድነት፣ በደስታና በትህትና እንዲኖሩ ለማበረታታት

መግቢያ

የፊልጵስዩስ መልእክት የተጻፈው በክርስቶስ ኢየሱስ በፊልጵስዩስ ላሉት ቅዱሳን ነው(ፊልጵ.1፥1)። ፊልጵስዩስ በጥንት የክርስትና ታሪክ ሐዋርያው ጳውሎስ የክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንን የመሰረተባት በአውሮፓ ምድር የመጀመሪያዋ ከተማ በመሆን ልዩ ታሪክ አላት። ቤተ ክርስቲያኒቱ ትንሽ ብትሆንም፤ በቁሳዊ ነገሮች ድሀ ብትሆንም በቸርነቷና ለሐዋርያው ጳውሎስ አገልግሎት ድጋፍ ማድረጓ አንዱ መለያዋ ነበር።

መልዕክቱን የማጥናት አስፈላጊነት

  • በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እውነተኛ ደስታን እንድናገኝ ስለሚያስተምረን
  • የክርስቶስን የትሕትና አርአያነትን ስለሚያሳየን
  • ለመንፈሳዊ ዕድገትና ብስለት ስለ ሚያበረታታ
  • በእግዚአብሔር ሰላም ጭንቀትን እንድናሸንፍ ስለሚረዳን
  • የተዋሓደ የአማኞችን የአንድነት ውበትን ስለሚያስተምር
  • ሓሳባችን ወደ መልካምና ንፁህ ወደ ሆነው በመቅረጽ የመከራን ግንዛቤ በወንጌል ስለሚለውጠው
  • የደስታችን ምንጭ የሆነው ጌታ በማንኛውም ዓይነት በምናልፍበት ሁኔታ ሁሉ ደስ ሊለን እንደሚችል ስለሚያስተምረን

የመልዕክቱ ዋና ሓሳብ

  • በክርስቶስ ላይ የተመሰረተ ደስተኛ ክርስቲያናዊ ኑሮ ላይ አፅንዖት ይሰጣል
  • በቤተክርስቲያን አንድነትንና ትህትናን ያበረታታል
  • በሐሰት ትምህርት ላይ ጥንቃቄ እንዲወሰድ ያሳስባል
  • የፊልጵስዩስ ሰዎች የአገልግሎት አጋርነት ጳውሎስ ያለውን አድናቆት ይገልጻል
ጥናት 1: “ሰላምታ“ ፊልጵስዩስ 1:1-2
ዓላማ

ለተቀባዮቹ ሰላምታ ለመስጠትና የእግዚአብሔርና የክርስቶስን የጸጋና የሰላም በረከቶችን ለማወጅ።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. የመልዕክቱ ጸሐፊው ማን ነው?
  2. በመልዕክቱ ከእርሱ ጋር የጠቀሰው ማንን ነው?
  3. ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው ከየት ነው?
  4. ጳውሎስ ራሱንና ጢሞቴዎስን የገለጸው እንዴት ነው?
  5. ጳውሎስ ራሱን ሐዋርያ በማለት ፈንታ እርሱንና አብሮት ያለውን አገልጋዮች(ባርያዎች) በማለት የጠራው ለምንድን ነው?
  6. መልዕክቱ የተጻፈው ለማን ነው?
  7. ጳውሎስ መልእክት ለሚጽፍላቸው ሰዎች ምን በማለት ይባርካቸዋል?
  8. “የክርስቶስ አገልጋዮች” (ባሪያዎች) የሚለው ቃል በጳውሎስ አመለካከት ምን ያሳያል?
  9. ጳውሎስ በሰላምታው ላይ ለምንድን ነው የቤተ ክርስቲያን ኤጲስቆጶሳትና ዲያቆናት የሚጨምረው?
  10. በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉ ቅዱሳን ሲል ምንን ያመለክታል?
  11. “ጸጋና ሰላም” የሚለው ሰላምታ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
  12. ጳውሎስ በዚህ መግቢያ ላይ የተናገረው ሐሳብ ከፊልጵስዩስ ሰዎች ጋር ስላለው ዝምድና ምን ሊያሳይ ይችላል?
  13. አማኞች ስለራሳቸው ምን አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል?
  14. ቤተ ክርስቲያን እርስ በርስ መተያየት ያለባት እንዴት ነው?
  15. ጸጋና ሰላም ክርስቲያናዊ ግንኙነቶችን ሊቀርጹ የሚችሉት እንዴት ነው?
  16. የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ከጳውሎስ ትሕትና ምን መማር ትችላለች?
  17. የክርስቶስ አገልጋይ ሆነህ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?
  18. በቤተክርስቲያንህ ውስጥ የመንፈስ አንድነት እንዲኖር አስተዋጽኦ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
  19. በክርስቶስ ኢየሱስ እንደ ቅዱሳን እንዴት መኖር ይቻላል?
  20. ጸጋንና ሰላምን ለሌሎች እንዴት ማካፈል ትችላለህ?
  21. ምን ተማርክ?
ጥናት 2: “ለቤተክርስትያን ምሥጋናና ጸሎት“ ፊልጵስዩስ 1፥3-11
ዓላማ

ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች ካቀረበው አስደሳች ጸሎት ለመማርና በምስጋና፣ በወንጌል አጋርነትና በመንፈሳዊ እድገት መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች ማሰቡን የጀመረው እንዴት ነው(ቁ.3)?
  2. የሚጸልየው በምን ዓይነት ስሜት ነው?(ቁ.4)
  3. የምስጋናው ምክንያት ምንድን ነው?
  4. ጳውሎስ በቁጥር 6 ላይ ምን ዓይነት መተማመን(confidence) እንዳለው ይናገራል?
  5. ጳውሎስ ፍቅሩን የገለጸው እንዴት ነው(ቁ.7-8)?
  6. የጳውሎስ የጸሎት ልመና ምንድን ነው(ቁ.9)?
  7. የዚህ እድገት ዓላማ ምንድን ነው(ቁ.10-11)?
  8. ጳውሎስ በጸሎቱ በደስታ የተሞላው ለምንድን ነው?
  9. “የወንጌል አጋርነት” ሲል ምን ማለት ነው?
  10. ቁጥር 6 ስለ እግዚአብሔር ሥራ በአማኞች መካከል ምን ያስተምራል?
  11. ፍቅርን በእውቀትና በማስተዋል አጉልቶ መናገሩን ለምን አስፈለገው?
  12. የጳውሎስ ጸሎት የመጨረሻ ግብ ምንድን ነው?
  13. አማኞች ከጳውሎስ የጸሎት ምሳሌ ምን መማር ይችላሉ?
  14. ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ያለውን አጋርነት እንዴት ማጠናከር ትችላለች?
  15. ፍቅርና ማስተዋል አብረው ማደግ የሚችሉት እንዴት ነው?
  16. አማኞች ከቁጥር 6 ምን ማረጋገጫ ማግኘት ይችላሉ?
  17. ለሌሎች አመስጋኝ ልብ ማዳበር የምትችለው እንዴት ነው?
  18. የወንጌልን ሥራ መደገፍ የምትችለው እንዴት ነው?
  19. በፍቅርና በማስተዋል ማደግ የምትችለው እንዴት ነው?
  20. በሕይወትህ እግዚአብሔርን እንዴት ማክበር ትችላለህ?
  21. ምን ተማርክ?
ጥናት 3: „የወንጌል መስፋት በመከራ“ ፊልጵስዩስ 1፥12-18
ዓላማ

የጳውሎስ መታሰር ወንጌልን ለማስፋፋት እና አማኞች ክርስቶስን በድፍረት እንዲሰብኩ ለማበረታታት እንዴት እንዳገለገለ ለመረዳት።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ የፊልጵስዩስ ሰዎች እንዲያውቁ የሚፈልገው ምንድን ነው(ቁ.12)?
  2. እንዴት ነው የሰፋው(ቁ.13)?
  3. ሌሎች አማኞች ምን ምላሽ ሰጡ?
  4. ከአንዳንድ ሰባኪዎች ጀርባ ምን ዓይነት ድብልቅልቅ ያለ መነሳሳት(Motive) አለ (ቁ.15-17)?
  5. የጳውሎስ ምላሽ ለሁሉም ምክንያቶች ምንድን ነው(ቁ.18)?
  6. ጳውሎስ የሰጠው ምላሽ ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው ነገሮች ምን ያሳያል?
  7. መከራ የእግዚአብሔርን ሥራ እንዴት ሊያራምድ ይችላል?
  8. በቤተመንግሥት ዘበኞች ዘንድ ወንጌል መሠራጨቱ ምንን ያሳያል?
  9. ጳውሎስ የውሸት ዓላማ ያላቸውን ሰዎች ያልተቆጣቸው ለምንድን ነው?
  10. ይህ ክፍል ስለ ደስታ ምን ያስተምራል?
  11. አማኞች በአገልግሎት ላይ የሚደርሰውን መከራ እንዴት ሊመለከቱት ይገባል?
  12. ሌሎች በተሳሳተ ዓላማ ሲሰብኩ ቤተ ክርስቲያን ምን ምላሽ መስጠት አለባት?
  13. ወንጌል በሌሎች ፈተናዎች እንዴት ሊሰፋ ወይም ሊሰራጭ ይችላል?
  14. አማኞች በመከራ ጊዜ ትክክለኛውን አመለካከት መያዝ የሚችሉት እንዴት ነው?
  15. በመከራ ጊዜ ደስተኛ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?
  16. በአንተ ምሳሌነት ሌሎችን ማነሳሳት የምትችለው እንዴት ነው?
  17. በአገልግሎት ላይ ከቅናት መራቅ የምትችለው እንዴት ነው?
  18. ሕይወትህን በወንጌል እድገት ላይ ማትኮር የምትችለው እንዴት ነው?
  19. ምን ተማርክ?
ጥናት 4: ለክርስቶስ መኖርና መሞት ፊልጵስዩስ 1፥19-26
ዓላማ

የጳውሎስን የመዳን እምነት፣ ለሕይወትና ለሞት ያለውን አመለካከትና ክርስቶስ በሁሉም ሁኔታዎች እንዲከበር ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ለመረዳት።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ ስለ መዳኑ ውጤት ምን ይላል?
  2. ጳውሎስ በጉጉት የሚጠብቀው ምንድን ነው?
  3. ጳውሎስ የሕይወቱን ዓላማ ጠቅለል አድርጎ የገለጸው እንዴት ነው(ቁ.21)?
  4. ጳውሎስ ፍሬያማ ሥራን የሚመለከተው እንዴት ነው(ቁ.22)?
  5. ጳውሎስ የገለጸው የትኛውን ውስጣዊ ግጭት ነው(ቁ.23-24)?
  6. ጳውሎስ በቁጥር 25 ላይ ስለምን ነገር ይተማመናል?
  7. የአገልግሎት ቀጣይነት ምንድነው የሚሆነው?
  8. ጸሎትና የመንፈስ እርዳታ መዳንን የሚያመጣው እንዴት ነው?
  9. የጳውሎስ ጉጉት ምን ያሳያል?
  10. “መኖር ክርስቶስ ነው” ሲል ምን ማለቱ ነው?
  11. መሞት ትርፍ ነው የሚለው የጳውሎስን እምነት በተመለከተ ምን ያሳያል?
  12. ጳውሎስ በአካል ለመቆየት የመረጠው ለምንድን ነው?
  13. አማኞች እንደ ጳውሎስ የሕይወትን ዓላማ ማግኘት የሚችሉት እንዴት ነው?
  14. እምነት የሰው ለሞት ያለውን አመለካከት ሊለውጠው የሚችለው እንዴት ነው?
  15. ቤተ ክርስቲያን በእምነት ለማደግ እርስ በርስ መደጋገፍ የምትችለው እንዴት ነው?
  16. አማኞች በዕለት ተዕለት ኑሮ ክርስቶስን እንዴት ሊያጎሉት ይችላሉ?
  17. ክርስቶስን የሕይወትህ ማዕከል ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
  18. ያለ ፍርሃት ሞትን እንዴት ማየት ይቻላል?
  19. ሌሎች በእምነት እንዲያድጉ መርዳት የምትችለው እንዴት ነው?
  20. ክርስቶስን በሰውነትህ እንዴት ልታከብረው ትችላለህ?
  21. ምን ተማርክ?
ጥናት 5: ለወንጌል እንደሚገባ መኖር ፊልጵስዩስ 1፥27-30
ዓላማ

አማኞችን በአንድነት፣ በፅናትና በመከራ በድፍረት በወንጌል ወጥ ያለው ህይወት እንዲኖሩ ጥሪ ለማድረግ።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ በቁጥር 27 ላይ የሚሰጠው ትእዛዝ ምንድን ነው?
  2. ጳውሎስ ቢጎበኛቸውም ባይጎበኛቸውም እውነቱ ምንድን ነው ይላል?
  3. ለተቃዋሚዎች ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል?
  4. በተቋዋሚዎች መረበሽ የማያስፈፈልገው ለምንድን ነው?
  5. የፊልጵስዩስ ሰዎች ምን ተሰጥቷቸዋል?
  6. ጳውሎስ መልእክት ለሚጽፍላቸው ወገኖች የሚያሳስባቸው ምንድን ነው?(ቁ.30)
  7. ለወንጌል እንደሚገባ መኖር ማለት ምን ማለት ነው?
  8. ለምንድን ነው ለአማኞች አንድነት አስፈላጊ የሆነው?
  9. ተቃዋሚዎችን አለመፍራት ፋይዳው ምንድን ነው?
  10. መከራ እንደ መልካም አጋጣሚ(privilage) ተደርጎ የተገለጸው ለምንድን ነው?
  11. የጳውሎስ ምሳሌ የፊልጵስዩስን አማኞች እንዴት ሊያባረታታቸው ይችላል?
  12. አማኞች ዛሬ ለወንጌል ብቁ ሆነው መኖር የሚችሉት እንዴት ነው?
  13. ቤተክርስትያን የመንፈስን አንድነት እንዴት መጠበቅ ትችላለች?
  14. አማኞች ለስደት መስጠት ያለባቸው ምላሽ ምን/እንዴት/መሆን አለበት?
  15. የሌሎች እምነት ጽናትህን የሚያጠናክረው እንዴት ነው?
  16. ለወንጌል የሚገባውን ሕይወት መምራት የምትችለው እንዴት ነው?
  17. ከሌሎች ጋር በእምነት አንድነት እንዲኖርህ ጥረት ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
  18. በድፍረት ተቃውሞን መቋቋም የምትችለው እንዴት ነው?
  19. ስለ ክርስቶስ መከራን እንዴት መቀበል እንዳለብህ ልትረዳ ትችላለህ?
  20. ምን ተማርክ?
ጥናት 6: አንድነት በትህትና ፊልጵስዩስ 2:1–4
ዓላማ

አማኞች የክርስቶስን አስተሳሰብ በማንፀባረቅ በትህትናና በፍቅር የመንፈስ አንድነትንና መተሳሰብን እንዲከተሉ ለማበረታታት።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ በቁ.1 ላይ ለአንድነት የሚያነሳሱትን የሚጠቅሳቸው አራት ነገሮች ምንድን ናቸው?
  2. ጳውሎስ ደስታው ሙሉ እንዲሆን የሚጠይቃቸው ምንድን ነው?
  3. ከየትኛው ዝምባሌ ነው መራቅ ያለባቸው?
  4. በዚህ ፈንታ ምን ማድረግ አለባቸው?
  5. በክርስቶስ ማበረታታት ማለት ምን ማለት ነው?
  6. ከፍቅር የሚመጣ መጽናናት በግንኙነቶች ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል?
  7. የመንፈስ ኅብረት ምንን ያመለክታል?
  8. ጳውሎስ በአንድ ሐሳብና ዓላማ መሆንን ጎላ አድርጎ የገለጸው ለምንድን ነው?
  9. እንዴት ነው ትሕትና ለአንድነት አስተዋጽኦ የሚያደርገው?
  10. አማኞች አንድነትን ማዳበር የሚችሉት እንዴት ነው?
  11. ትሕትና ግንኙነቶችን ሊለውጠው የሚችለው እንዴት ነው?
  12. ቤተ ክርስቲያን ራስ ወዳድነትን ማሸነፍ የምትችለው እንዴት ነው?
  13. አማኞች ይህን ትእዛዝ በተግባር ማሳየት የሚችሉት እንዴት ነው?
  14. በግንኙነትህ ውስጥ ትሕትናን መለማመድ የምትችለው እንዴት ነው?
  15. በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ከሌሎች ጋር የመንፈስ አንድነት እንዲኖር እንዴት መትጋት ትችላለህ?
  16. ለሌሎች አሳቢነት ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
  17. ከራስ ወዳድነት ምኞት መራቅ የምትችለው እንዴት ነው?
  18. ምን ተማርክ?
ጥናት 7: የክርስቶስ የትሕትና ምሳሌነት ፊልጵስዩስ 2፡5-11
ዓላማ

የክርስቶስ ራሱን ባዶ ማድረግና ከፍ ከፍ መደረግ ለአማኞች የትህትናና ታዛዥነት ከፍተኛ ምሳሌ እንደሆነ ለመረዳት።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. አማኞች ምን ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ተጠርተዋል?
  2. የክርስቶስ መልክ ሥጋ ከመልበሱ በፊት እንዴ ነበር?
  3. ከእግዚአብሔር ጋር እኩል መሆንን ያላሰበው ምንድን ነው?
  4. ክርስቶስ በምትኩ ምን አደረገ?
  5. የክርስቶስ ታዛዥነት እስከምን ድረስ ሄዷል?
  6. እግዚአብሄር ለትሕትናው የሰጠው ምላሽ ምን ነበር?
  7. ጉልበትና ምላስ ሁሉ ምን ያደርጋል?
  8. “ራሱን ባዶ አደረገ” ማለት ምን ማለት ነው?
  9. በዚህ ክፍል ውስጥ የመስቀሉ አስፈላጊነት ምንድን ነው?
  10. እግዚአብሄር ክርስቶስን ከፍ ያደረገው ለምንድን ነው?
  11. „ጒልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ“ሲል ስለ ኢየሱስ ጌትነት ምን ያሳያል?
  12. ይህ ክፍል አማኞችን ስለ እውነተኛ ታላቅነት ምን ያስተምራል?
  13. አማኞች የክርስቶስን ትሕትና ምሳሌ መከተል የሚችሉት እንዴት ነው?
  14. ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ታዛዥነት ማንጸባረቅ የምትችለው እንዴት ነው?
  15. እግዚአብሄር ኢየሱስን ከፍ ከፍ የማድረጉ ምሳሌ አማኞች አንድ ሆነው እንዲቀጥሉና እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ የሚረዳቸው እንዴት ነው?
  16. ትሕትና እግዚአብሄር ሕይወታችንን ከፍ ከፍ ወደ ሚያደርገው መንፈሳዊ ከፍታ ለመድረስ እንዴት ያስችላል?
  17. በፊልጵስዩስ 2 ላይ እንደተገለጸው፣ እግዚአብሄር ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉትን ከፍ እንደሚያደርጋቸው የክርስቶስ ምሳሌ የሚያሳየው እንዴት ነው?
  18. የክርስቶስን አስተሳሰብ ማዳበር የምትችለው እንዴት ነው?
  19. የክርስቶስን የአገልግሎት ምሳሌ መከተል የምትችለው እንዴት ነው?
  20. ክርስቶስን በህይወትህ ከፍ ከፍ እንዲል ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
  21. እግዚአብሔርን በትሕትና ማክበር የምትችለው እንዴት ነው?
  22. ምን ተማርክ?
ጥናት 8: እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበራላችሁ ፊልጵስዩስ 2፡12-18
ዓላማ

አማኞች በጨለማ ዓለም እንደ ከዋክብት እየበሩ መዳናቸውን በመታዘዝ እንዲሠሩና ያለ ነቀፋ እንዲኖሩ ለማበረታታት።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ የአማኞችን መታዘዝ እንዴት ይገልጸዋል?
  2. ምን እንዲያደርጉ ያዛቸዋል?
  3. ቁጥር 13 ስለ እግዚአብሄር ሚና ምን ያሳያል?
  4. ማስወገድ ያለባቸው ምንድን ነው?
  5. ምን ዓይነት ሰዎች መሆን አለባቸው?
  6. በዚያ ትውልድ ምን ሊያደርጉ ተጠርተዋል?
  7. ጳውሎስ ታማኝነታቸውን እንዴት ይመለከተዋል?
  8. „የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ“ ሲል ምን ማለቱ ነው?
  9. “ፍርሃትና መንቀጥቀጥ” የተጠቀሰው ለምንድን ነው?
  10. የእግዚአብሔር የውስጥ ሥራ ምን ዋስትና ይሰጣል?
  11. ጳውሎስ ማጉረምረም እንዳይኖር የሚያስጠነቅቀው ለምንድን ነው?
  12. የአማኞች መብራት በዓለም እንዴት ነው?
  13. አማኞች ከእግዚአብሄር ሥራ ጋር መተባበር የሚችሉት እንዴት ነው?
  14. ቤተ ክርስቲያን በሌሎች ፊት መብራት የምትችለው እንዴት ነው?
  15. ምስጋና ማጉረምረምን የሚተካው እንዴት ነው?
  16. በእምነት መጽናት ለሌሎች ደስታ ሊያስገኝ የሚችለው እንዴት ነው?
  17. ማዳንህን በታማኝነት መሥራት የምትችለው እንዴት ነው?
  18. በዕለት ተዕለት ምርጫዎችህ ለእግዚአብሄር አክብሮት እንዳለህ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
  19. በአካባቢህ እንደ ከዋክብት ማብራት የምትችለው እንዴት ነው?
  20. ማጉረምረምን በደስታ መተካት የምትችለው እንዴት ነው?
  21. ምን ተማርክ?
ጥናት 9: የታማኝነት አገልግሎት ምሳሌ ፊልጵስዩስ 2፥19-30
ዓላማ

በጢሞቴዎስና በአፍሮዲጡ ምሳሌ አማካኝነት የታማኝ አገልጋዮችን ባሕርያት ለማጉላትና አማኞች በአንድ ልብ እንዲያገለግሉ ለማበረታታት።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ በቅርቡ ምን እንደሚያደርግ ተስፋ ያደርጋል?
  2. ጳውሎስ በጢሞቴዎስ ላይ የነበረው መተማመን ለምንድን ነው?
  3. ሌሎች ከጢሞቴዎስ የሚለዩት እንዴት ነው?
  4. ጢሞቴዎስ ራሱን ያረጋገጠው እንዴት ነበር?
  5. የጳውሎስ ዕቅድ ምንድን ነበር?
  6. ጳውሎስ ሌላ ማንን ይጠቅሳል?
  7. አፍሮዲጡ ለምን ተጨነቀ?
  8. ጳውሎስ ስለ መዳኑ ምን ይላል?
  9. ጳውሎስ መልሶ የላከው ለምንድን ነው?
  10. እንዴት ሊቀበሉት ይገባል?
  11. የጢሞቴዎስ ምሳሌ ስለ አገልግሎት ምን ያስተምራል?
  12. የአፍሮዲጡ ምሳሌነት ሕይወቱን መሥዋዕት እስከመሆን ድረስ መሰጠት ምን ያሳያል?
  13. ጳውሎስ ታማኝነታቸውን ጎላ አድርጎ የገለጸው ለምንድን ነው?
  14. ይህ ክፍል ስለ አገልግሎት አጋርነት ምን ያስተምራል?
  15. አማኞች እንደ ጢሞቴዎስ በታማኝነት ማገልገል የሚችሉት እንዴት ነው?
  16. ቤተ ክርስቲያን መስዋዕት በመክፈል የሚያገለግሉትን ወገኖች እንዴት ማክበር ይገባታል?
  17. አማኞች አንዳቸው የሌላውን ሸክም መሸከም የሚችሉት እንዴት ነው?
  18. አገልግሎት ለሌሎች ደስታ ሊያስገኝ የሚችለው እንዴት ነው?
  19. ለሌሎች እውነተኛ አሳቢነት ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
  20. ወንጌልን በታማኝነት ማገልገል የምትችለው እንዴት ነው?
  21. እግዚአብሔርን በማገልገል ለደከሙ ወይም ተስፋ ለቆረጡ አማኞች ተግባራዊ በሆነ መንገድ እንዴት ልታበረታታቸው ትችላለህ?
  22. የጢሞቴዎስንና የአፍሮዲጦስን ምሳሌ መከተል የምትችለው እንዴት ነው?
  23. ምን ተማርክ?
ጥናት 10: ክርስቶስን የማወቅ ልቀት ፊልጵስዩስ 3፥1-11
ዓላማ

በሰው ሥራ ላይ የተሳሳተ መተማመንን ለማስጠንቀቅና ክርስቶስን እንደ ጌታ የማወቅ የላቀ ዋጋ ያለው መሆኑን ለማጉላት።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ በቁጥር 1 ላይ እንደገና የሚደግመው ትዕዛዝ ምንድንነው?
  2. የሚሰጠው ማስጠንቀቅያ ምንድን ነው?
  3. እውነተኛው መገረዝ እነማን ናቸው?
  4. ጳውሎስ የሚዘረዝራቸው መንፈሳዊ መመዘኛዎች ምንድን ናቸው?
  5. ጳውሎስ በአንድ ወቅት እንደ ትርፍ ያስባቸው የነበሩ ነገሮች አሁን እንዴት ይመለከታቸዋል?
  6. ከሁሉ በላይ ዋጋ የሚሰጠው ምንድን ነው?
  7. ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ሲነፀጸር ምንድን ነው ይላል?
  8. ጳውሎስ የሚፈልገው ምን ዓይነት ጽድቅ ነው?
  9. ከሁሉም በላይ ለማወቅ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  10. የሚጠብቀው ግብ ምንድን ነው?
  11. በሰዎች ስኬት መታመን ምን አደጋ አለው?
  12. ጳውሎስ የቀድሞ ጥቅሙን ኪሳራ ብሎ የገለጸው ለምንድን ነው?
  13. “ክርስቶስን ማወቅ” ሲል ምን ማለቱ ነው?
  14. በክርስቶስ መከራ መካፈል ሲል ምን ማለቱ ነው?
  15. ጳውሎስ የትንሣኤን ተስፋ እንዲከታተል ያነሳሳው ምንድን ነው?
  16. አማኞች ከከንቱ መተማመን መጠበቅ የሚችሉት እንዴት ነው?
  17. ክርስቶስን ማወቅ ከሁሉ የሚበልጠው እንዴት ነው?
  18. አማኞች በየቀኑ የትንሣኤን ኃይል እንዴት ሊለማመዱ ይችላሉ?
  19. መከራ እምነትን እንዴት ሊያጠነክር ይችላል?
  20. በፊልጲስዩስ 3፥9–11 መሠረት ስለ አማኝ መንፈሳዊ ህይወት ከዚህ ልትረዳ የምትችልው ምንድን ነው?
  21. በራስ የመተማመን ስሜትን እንዴት መተው ይቻላል?
  22. ክርስቶስ ከሁሉ በላይ መሆኑን በተግባራዊ መንገድ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
  23. በመከራ ውስጥ እንዴት ደስ ሊልህ ይችላል?
  24. ምን ተማርክ?
ጥናት 11: ወደ ግብ ማትኮር ፊልጵስዩስ 3፥12-21
ዓላማ

አማኞች ትኩረታቸውን በክርስቶስ የእግዚአብሔር ሰማያዊ ጥሪ ላይ በማድረግ መንፈሳዊ ብስለት እንዲከተሉ ለማበረታታት።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊ ሁኔታው ምን ይላል?
  2. ጳውሎስ ወደፊት በመግፋት ለመቀጠል ምክንያት የሚያደርገው ወይም የሚያነሳሳው ምንድን ነው?
  3. ጳውሎስ ትኩረቱን የሚገልጸው እንዴት ነው?
  4. የበሰሱ አማኞች ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል?(ቁ.15)?
  5. እንዴት ነው አማኞች መኖር ያለባቸው?(ቁ.16-17)
  6. ጳውሎስ የሚሰጠው ማስጠንቀቂያ ምንድን ነው?(ቁ.18-19)?
  7. የአማኝ እውነተኛ ዜግነት ምንድን ነው?
  8. የሚከሰተው ለውጥ ምንድን ነው?
  9. በመንፈሳዊ ሕይወት„ወደ ግቡ እፈጥናለሁ„ማለት ምንድን ነው የሚያስተምረው?
  10. ለምንድን ነው አማኞች የኋላቸውን መርሳት ያለባቸው?
  11. ጳውሎስ እየተናገረለት ያለው ሽልማት ምንድን ነው?
  12. የመስቀሉ ጠላቶች ሆነው መኖር ምን አደጋ አለው?
  13. ጽናትን የሚያበረታታ የትኛው ተስፋ ነው?
  14. አማኞች መንፈሳዊ ብስለትን እንዴት መከታተል ይችላሉ?
  15. ቤተ ክርስቲያን ከዓለማዊ ትኩረት መጠበቅ የምትችለው እንዴት ነው?
  16. አማኞች በፈተና ውስጥ ጸንተው መኖር የሚችሉት እንዴት ነው?
  17. የትንሣኤ ተስፋ የዕለት ተዕለት ሕይወትን ሊለውጠው የሚችለው እንዴት ነው?
  18. እንዴት ነው ወደ እግዚአብሄር ግብ መፍጠን የሚቻለው?
  19. ታማኝ አማኞችን መምሰል የምትችለው እንዴት ነው?
  20. ልብህ በሰማያዊ ነገሮች ላይ እንዲያተኩር የሚረዱህ ልምምዶች ምንድናቸው?
  21. ራስህን ለለውጥ እንዴት ማዘጋጀት ትችላለህ?
  22. ምን ተማርክ?
ጥናት 12: በጌታ ጸንቶ በሰላም መኖር ፊልጵስዩስ 4:1-9
ዓላማ

አማኞች በአንድነት ጸንተው እንዲቆሙ፣ በጌታ እንዲደሰቱ፣ ከምስጋና ጋር እንዲጸልዩና በአምላካዊ አስተሳሰብ እንዲጸኑ ለማስተማር።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ በቁጥር 1 ላይ የሚሰጣቸው ትእዛዝ ምንድን ነው?
  2. ጳውሎስ በቁ.2-3 ላይ ስለ ምን ግጭት ነው እየተናገረ ያለው? ለምን?
  3. ጳውሎስ በ ቁ.4 ላይ ደጋግሞ የሚሰጠው ትእዛዝ ምንድን ነው?
  4. አማኞች በምን እንዲታወቁ መፍቀድ አለባቸው?
  5. በመጨነቅ ፈንታ ምን ማድረግ አለባቸው?
  6. ውጤቱ ምን ይሆናል?
  7. ጳውሎስ ምን እንዲያስቡ ያዛቸዋል?
  8. በቁ.9 ላይ ምን እያለ ያሳስባቸዋል?
  9. በጌታ ጸንቶ መቆም ሲል ምን ማለት ነው?
  10. ለምንድን ነው በጌታ ደስ ይበላችሁ ብሎ የሚደጋግመው?
  11. ጸሎት ጭንቀትን ሊተካ የሚችለው እንዴት ነው?
  12. ስለ አምላካዊ ነገሮች ማሰብ ምን ትርጉም አለው?
  13. የጳውሎስን ምሳሌ መከተል እንዴት ሰላም ሊሰጥ ይችላል?
  14. አማኞች ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚችሉት እንዴት ነው?
  15. ደስታ የአኗኗር ዘይቤ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
  16. አማኞች ከጭንቀት መጠበቅ የሚችሉት እንዴት ነው?
  17. አማኞች በዲሲፕሊን ድርሻቸውን ለመወጣት አእምሮአቸውን እንዴት ማሰልጠን (train) ማድረግ ይችላሉ?
  18. በእምነት ጸንተህ መቆም የምትችለው እንዴት ነው?
  19. ጭንቀትን ወደ ጸሎት መቀየር የምትችለው እንዴት ነው?
  20. አእምሮህን ንጹሕና ሰላማዊ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
  21. ለሌሎች ሰላም ለማምጣት እንዴት መርዳት ትችላላህ?
  22. ምን ተማርክ?
ጥናት 13: በክርስቶስ እርካታና ልግስና ፊልጵስዩስ 4፥10-20
ዓላማ

በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ የመርካትን ምስጢርና የታማኝ ልግስና በረከቶችን መማር።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ እንዲደሰት ያደረገው ምንድን ነው?
  2. ጳውሎስ ስለ ደስታው ግልጽ የሚያደርገው ምንድን ነው?
  3. ምን ዓይነት ሁኔታዎች አጋጥመውታል?
  4. ጳውሎስ በ ቁ.13 ላይ የሚናገረው እውነት ምንድን ነው?
  5. የፊልጵስዩስ ሰዎች በችግሩ ውስጥ የተካፈሉት እንዴት ነበር?
  6. ከዚህ በፊት የመስጠት ሪከርዳቸው ምን ይመስል ነበር?
  7. ጳውሎስ በመስጠታቸው የሚፈልገው ምንድን ነው?
  8. ሥጦታቸው እንዴት ይገልጸዋል?
  9. ጳውሎስ በቁጥር 19 ላይ ምን ተስፋ ይሰጣል?
  10. ጳውሎስ ይህን ክፍል እንዴት ይደመድመዋል?
  11. የመርካት ምስጢር ምንድን ነው?
  12. ጳውሎስ ስለ መስጠት የሚያስተምረው ምንድን ነው?
  13. የእግዚአብሔርን አሰጣጥን በሚመለከት ምን ይላል?
  14. ጳውሎስ በመጨረሻ ላይ ለምንድንነው እግዚአብሔርን የሚያወድሰው?
  15. እንዴት ነው አማኞች ያለኝ/ኑሮየ/ ይበቃኛል ማለት ሊማሩ የሚችሉት?
  16. ልግስና አምልኮ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
  17. አማኞች የእግዚአብሔርን አቅርቦት (God’s provision) እንዴት ሊለማመዱ ይችላሉ?
  18. ቤተ ክርስቲያን በመስጠት ረገድ አጋርነትን እንዴት መለማመድ ትችላለች?
  19. እርካታን(ያለኝ ይበቃኛል)ማዳበር የምትችለው እንዴት ነው?
  20. በየዕለቱ በክርስቶስ ጥንካሬ መታመን የምትችለው እንዴት ነው?
  21. ልግስናን እንዴት መለማመድ ትችላለህ?
  22. በመስጠት እግዚአብሔርን ማክበር የምትችለው እንዴት ነው?
  23. ምን ተማርክ?
ጥናት 14: የመጨረሻ ሰላምታ ፊልጵስዩስ 4፥21-23
ዓላማ

በጳውሎስ፣ የአገልግሎት አጋሮቹና በፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን የጠበቀ ትስስር በጋራ ሰላምታና እውቅና ለማረጋገጥ።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ ሰላምታ የላከው ለማን ነው?
  2. ሌላስ አብሮ ሰላምታ ማን ይልካል?
  3. ጳውሎስ መልእክቱን እንዴት ይዘጋዋል?
  4. “ቅዱሳን ሁሉ” ምንን ያመለክታል?
  5. “የቄሳር ቤት” ስለ ወንጌል ምን ያሳያል?
  6. ለምንድን ነው ጳውሎስ ጸጋ በማለት መልእክቱን የሚያጠቃልለው?
  7. አማኞች ሰላምታ መሰጣጠትን በሚመለከት የክርስቶስን አካል አንድነት እሴት(value) ሊመለከቱት የሚገባቸው እንዴት ነው?
  8. ጸጋ የዕለት ተዕለት ሕይወትን እንዴት ሊቀርጽ ይችላል?
  9. ለሁሉም አማኞች ፍቅር ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
  10. ፀጋ ሕብረታችሁን(ግንኙነታችሁን) እንዲቆጣጠር ከአንተ የሚጠበቀውን ድርሻህን ለመወጣት ምን ማድረግ እንዳለብህ ልትገነዘብ ትችላለህ?
  11. ወንጌል እንዲስፋፋ ለመርዳት ምን ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ ትችላለህ?
  12. በክርስቶስ ጸጋ ላይ እንዴት ማረፍ ትችላለህ?
  13. ምን ተማርክ?
ጥናት 15: በክርስቶስ ደስታ፣ አንድነትና ጥንካሬ! ማጠቃለያ
ዓላማ

በአጠቃላይ መልእክቱን በማሰላሰል ከሕይወት ጋር ማጋናኘትን።

የመወያያ ጥያቄዎች
  1. ጳውሎስ መልእክቱ የጻፈው ከየት ነው?(የጻፈበት ቦታና የነበረው ሁኔታ)
  2. ከእርሱ ጋር ማን ተጠቅሰዋል?
  3. የመልእክቱ ቃና(tone) ምንድን ነው?
  4. የመልእክቱ ዋና ጭብጦች ምንድናቸው?
  5. የፊልጵስዩስ መልእክት ስለ ደስታ ምንድን ነው የሚያስተምረው?
  6. ስለ አንድነት ምን ያስተምራል?
  7. ባለህ ነገር ስለመርካት ምን ያስተምራል?
  8. ስለ ጸጋ ምን ያስተምራል?
  9. አማኞች በዛሬው ጊዜ በፊልጵስዩስ ሰዎች በተጻፈው መልእክት እንዴት መኖር ይችላሉ?
  10. ቤተክርስቲያን መልእክቱን በሕይወት በሥራ ላይ በማዋል እንዴት ልትለማመድ ትችላለች?
  11. የክርስቶስ ምሳሌ የአማኞችን ሕይወት ሊቀርጽ የሚችለው እንዴት ነው?
  12. ሁሉ ጊዜ እንዴት ደስ ሊልህ ይችላል?
  13. በትሕትና ማገልገል የምትችለው እንዴት ነው?
  14. በሁሉም ነገር ረክተህ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?
  15. ዕለት ተዕለት በጸጋ ላይ እንዴት መታመን ትችላላችሁ?
  16. ምን ተማርክ?
ማሳሰብያ: ይህ የአገልግሎት ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አገልግሎት እንደመሆኑ መጠን በየሳምንቱ በሚኖረው ፕሮግራም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ጸሎት እንዲደረግ። የጸሎቱ ትኩረትም የበለጠ በተጠናው ጥናትና ሊጠና ባለው ጥናት ላይ እንዲሆን።