35 Jahre Evangelische Gemeinde: Ein Fest des Dankes und Rückblicks

Vom 12. bis 13. April feierte unsere Evangelische Gemeinde ihr 35-jähriges Bestehen mit einer beeindruckenden und vielfältigen Jubiläumsfeier. Dieses besondere Jubiläum war eine wunderbare Gelegenheit, innezuhalten, auf das Werk Gottes zurückzublicken und gemeinsam Danke zu sagen.

Das Programm spiegelte die verschiedenen Facetten des Gemeindelebens wider. Ein Highlight war die Teilnahme ehemaliger Lobpreisleiter, die die musikalische Reise der Gemeinde über die Jahrzehnte lebendig machten. Ebenso wertvoll war die Anwesenheit der Geschwister, die vor 35 Jahren mutig den Grundstein der Gemeinde legten. Ihre Zeugnisse gaben tiefe Einblicke in die Anfänge und das feste Fundament des Glaubens.

Besonders bewegend war das Gespräch zwischen drei Generationen. Zeitzeugen berichteten, wie sie zur Gemeinde fanden, hier Jesus Christus kennenlernten und im Glauben wuchsen. Zu hören, dass heute ihre Kinder aktiv in derselben Gemeinde dienen und den Glauben weitertragen, ist ein starker Beweis für die Beständigkeit und Fruchtbarkeit der Arbeit der letzten 35 Jahre.

Über allem stand der tiefe Dank an Gott für seine Gnade, die die Gemeinde durch alle Zeiten begleitet hat. Dass die Gemeinde heute so lebendig dasteht, wird als klares Zeichen Seiner Treue und Barmherzigkeit verstanden. Ihm allein gebührt die Ehre für alles, was Er getan hat und in Zukunft tun wird.

የ35 ዓመታት የእግዚአብሔር ታማኝነት፡

ከApril 12 እስከ 13 ባሉት ቀናት የፍራንክፈርት ኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን 35ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሏን ደማቅና የተለያየ ዝግጅት ባለው ሁኔታ አክብራለች። ይህ ልዩ የኢዮቤልዩ በዓል ቆም ብለን የእግዚአብሔርን ሥራ ወደ ኋላ ለመመልከት እና በአንድነት ሆነን ከልብ እርሱን ለማመስገን ግሩም አጋጣሚ ነበር።
የዕለቱ ፕሮግራም የቤተ ክርስቲያናችንን የተለያዩ የአገልግሎት ገጽታዎች የሚያንጸባርቅ ነበር። በተለይም ቀደምት የአምልኮ መሪዎች መገኘታቸውና ላለፉት አሥርተ ዓመታት የነበረውን የዝማሬ ጉዟችንንና የጠለቀ የአምልኮ ጊዜያትን በድጋሚ ሕያው ማድረጋቸው የዝግጅቱ ድምቀት ነበር። ከ35 ዓመታት በፊት በድፍረት የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረት የጣሉ ወንድሞችና እህቶች መገኘትም እጅግ ውድ ነበር። የእነርሱ የግል ምስክርነት ስለተባረከው ጅማሬያችንና ስለ እምነታችን ጽኑ መሠረት ጥልቅ ግንዛቤ እንድናገኝ አድርጎናል።
በሦስት ትውልዶች መካከል የነበረው የልምድ ልውውጥ እጅግ ልብ የሚነካ ነበር። ታሪክ አዋቂዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደመጡ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን በግል እንዴት እንዳወቁና በመንፈስ ቅዱስ እንዴት እንዳደጉ መስክረዋል። ዛሬ ልጆቻቸው በዚያችው ቤተ ክርስቲያን በንቃት እያገለገሉና የእምነትን እሳት እያስተላለፉ መሆናቸውን መስማትና ማየት፣ ላለፉት 35 ዓመታት የተሠራው መንፈሳዊ ሥራ ዘላቂነትና ፍሬያማነት ጠንካራ ማረጋገጫ ነው።
ከሁሉ በላይ ቤተ ክርስቲያናችንን በዘመናት ሁሉ ለጠበቃት ለእግዚአብሔር ጸጋ ጥልቅ ምሥጋና ቀርቧል። ዛሬ በፍራንክፈርት ከተማ እንዲህ ሕያው የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሆነን መቆማችን የታማኝነቱና የምሕረቱ ግልጽ ምልክት ነው። እስካሁን ላደረገውና ወደፊትም ለሚያደርገው ነገር ሁሉ ክብር ለእርሱ ብቻ ይሁን!